ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከጌታ ዘንድ ነው።
ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።
ርዳታዬ የሚመጣው ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ነው።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግሮቻችን በአደባባዮችሽ ቆሙ።
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።
እናንተ ሰማይንና ምድርን በሠራ ጌታ የተባረካችሁ ሁኑ።
ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በጌታ ስም ነው።
ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ምሥጢር፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
እኔ አምላክህ ጌታ ነኝ፦ “አትፍራ፥ እረዳሃለሁ” ብዬ ቀኝህን የያዝኩ።
ጌታ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘለዓለምም በማይረሳ ውርደት ይዋረዳሉ።
እስራኤል ሆይ! በእኔ በረዳትህ ላይ በመነሣትህ ጠፍተሀል።
ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንላለን።