Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 124 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


1 የዳዊት የዕርገት መዝሙር።

1 የዳዊት የዕርገት መዝሙር። ጌታ ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦

2 ጌታ ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥

3 ቁጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፥

4 በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ወራጅ ውኃ ባለፈ ነበር፥

5 በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።

6 ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን ጌታ ይመስገን።

7 ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፥ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።

8 ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በጌታ ስም ነው።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች