8 ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በጌታ ስም ነው።
8 የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣ የእግዚአብሔር ስም ረዳታችን ነው።
8 ይህንንም ርዳታ ያገኘነው ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከጌታ ዘንድ ነው።
እነርሱም በሰሙ ጊዜ በአንድ ልብ ሆነው ውፍደ እፍዚአብሔር ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤ እንዲህም አሉ “ጌታ ሆይ! አንተ ሰማዩንና ምድሩን ባሕሩንም በእነርሱም የሚኖረውን ሁሉ የፈጠርህ፥
‘አቤቱ ጌታ ሆይ! ወዮ! እነሆ፥ በእውነት አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ለአንተም ከቶ የሚሳንህ ምንም ነገር የለም።
ሰማይንና ምድርን የሠራ ጌታ ከጽዮን ይባርክህ።
እናንተ ሰማይንና ምድርን በሠራ ጌታ የተባረካችሁ ሁኑ።
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።
አንተ ብቻህን ጌታ ነህ፥ ሰማይንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድርንና በእርሷ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጠርህ፥ ለሁሉም ሕይወትን ሰጠሃቸው፤ የሰማይ ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ።
እነኚህ በሠረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፥ እኛ ግን በአምላካችን በጌታ ስም ከፍ ከፍ እንላለን።