ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሣ፥ ወደ ኤልያሺብ ልጅ ወደ ይሆሐናን ክፍል ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹ አለመታመን አዝኖ ነበርና በዚያ ገብቶ እንጀራ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም።
መዝሙር 119:53 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕግህን ከተዉ ከኃጢአተኞች የተነሣ ኀዘን ያዘኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕግህን ከተዉ ክፉዎች የተነሣ፣ ቍጣ ወረረኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ሕግህን ሲተላለፉ በማየቴ በብርቱ ተቈጣሁ። |
ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሣ፥ ወደ ኤልያሺብ ልጅ ወደ ይሆሐናን ክፍል ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹ አለመታመን አዝኖ ነበርና በዚያ ገብቶ እንጀራ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም።
ትእዛዝህን ለማፍረስ፥ ርኩስ ሥራን ከሚሠሩ ከእነዚህም ሕዝቦች ጋር ለመጋባት እንመለሳለንን? አንተስ ትሩፋን የሌለንና የማናመልጥ እስክንሆን ድረስ እንድታጠፋን አትቆጣምን?
ከእነርሱም ጋር ተከራከርሁ፥ ረገምኋቸውም፥ ከእነርሱም አያሌዎቹን መታሁ፥ ጠጉራቸውንም ነጨሁ፥ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፦ ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለእናንተና ለልጆቻችሁ አትውሰዱ።
እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።
እንደገና ስመጣ በእናንተ ፊት አምላኬ ያዋርደኝ ይሆን እያልኩ፥ ከዚህ በፊት ስለ ሠሩት ኃጢአትና ስለ ፈጸሙትም ርኩሰት፥ ዝሙትና መዳራት ንስሓ ሳይገቡ ቀርተው እንዳላዝን እፈራለሁ።