ኤርምያስ 13:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የጌታም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ እጅግ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ባትሰሙ ግን፣ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ፣ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔር መንጋ ተማርኳልና፣ ዐይኔ አምርሮ ያለቅሳል፤ እንባዬም እንደ ጐርፍ ይወርዳል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 አናዳምጥም ብትሉ ግን ስለ ትዕቢታችሁ ተደብቄ አለቅሳለሁ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ ምርኮኞች ሆነው በመወሰዳቸውም ምርር ብዬ አለቅሳለሁ፤ እንባዬም ባለማቋረጥ ይፈስሳል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተሰብሮአልና ዐይኔ ታነባለች፤ እንባንም ታፈስሳለች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፥ የእግዚአብሔርም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች። ምዕራፉን ተመልከት |