Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 13:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከእነርሱም ጋር ተከራከርሁ፥ ረገምኋቸውም፥ ከእነርሱም አያሌዎቹን መታሁ፥ ጠጉራቸውንም ነጨሁ፥ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፦ ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለእናንተና ለልጆቻችሁ አትውሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እኔም ገሠጽኋቸው፤ ርግማንም አወረድሁባቸው። አንዳንዶቹን መታኋቸው፤ ጠጕራቸውንም ነጨሁ። በእግዚአብሔር ስም እንዲህ ስል አማልኋቸው፤ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እነዚህንም ሰዎች ገሠጽኳቸው፤ ረገምኳቸውም፤ ደብድቤም ጠጒራቸውን ነጨሁ፤ ከዚህም በኋላ እነርሱም ሆኑ ልጆቻቸው ከባዕዳን ሕዝብ ጋር ጋብቻ እንዳይፈጽሙ በእግዚአብሔር ስም አስማልኳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እነ​ር​ሱ​ንም ተቈ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ረገ​ም​ኋ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዐያ​ሌ​ዎ​ቹን መታሁ፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም ነጨሁ፤ እን​ዲ​ህም ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ል​ኋ​ቸው፥ “ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ከእነርሱም ጋር ተከራከርሁ፥ ረገምኋቸውም፥ ከእነርሱም አያሌዎቹን መታሁ፥ ጠጉራቸውንም ነጨሁ፥ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፦ ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለእናንተና ለልጆቻችሁ አትውሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 13:25
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከይሁዳም ታላላቆች ጋር ተከራከርሁና፦ ይህ የምታደርጉት ክፉ ነገር ምንድነው? የሰንበትንስ ቀን ታረክሳላችሁን?


ዕዝራም ተነሣ፤ አለቆቹን፥ ካህናቱን፥ ሌዋውያኑንና እስራኤልንም ሁሉ እንደዚህ ቃል እንዲያደርጉ አስማላቸው፥ እነርሱም ማሉ።


ከእነርሱም ጋር አትጋባ፥ ሴት ልጅህን ለወንድ ልጁ አትስጥ፥ ሴት ልጁንም ለወንድ ልጅህ አትውሰድ፤


እኔም፦ የእግዚአብሔር ቤት ስለምን ተተወ? ብዬ ከአለቆቹ ጋር ተከራከርሁ። ሰበሰብኋቸውም፥ በየስፍራቸውም አቆምኋቸው።


ጀርባዬን ለገራፊዎች፥ ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ፤ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።


ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያመሰግናሉ፥ ሕግ ጠባቂዎች ግን ይቃወሟቸዋል።


ኃጢአተኛ ሰው በፊቱ የተናቀ፥ ጌታን የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ቢጎዳም የማለውን የማይከዳ።


ደግሞም ልብሴን አራገፍሁና፦ “ይህን ቃል የማይፈጽመውን ሰው እግዚአብሔር ከቤቱና ከንብረቱ እንደዚሁ ያራግፈው፤ እንዲሁም የተራገፈና ባዶ ይሁን” አልሁ። ጉባኤውም ሁሉ፦ “አሜን” አሉና ጌታን አመሰገኑ፤ ሕዝቡ ቃል ኪዳኑ አደረጉ።


የአምላክህን ሕግና የንጉሡን ትእዛዝ በማያደርግ በማንም ላይ ሞት ወይም ስደት ወይም ንብረት መወረስ ወይም ግዞት በፅኑ ይፈረድበት።”


ጌታ እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱንም አምልክ፥ በስሙም ማል።


ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንድ ልጆችህ ብትወስድ፥ ሴቶች ልጆቻቸው አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ልጆችህን ከአምላኮቻቸው ጋር እንዲያመነዝሩ ያደርጓቸዋል።


እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ ብትጠጉ፥ ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ እናንተም ከእነርሱ እነርሱም ከእናንተ ጋር በጋብቻ ቢተሳሰሩ፥


ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው።


ከልጆቻቸውም እኩሌቶቹ በአዛጦን ቋንቋ ይናገሩ ነበር፥ በአይሁድም ቋንቋ መናገር አያውቁም ነበር።


ሕግህን ከተዉ ከኃጢአተኞች የተነሣ ኀዘን ያዘኝ።


እኔም ጩኸታቸውንና እነዚህን ቃላት በሰማሁ ጊዜ እጅግ ተቆጣሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች