የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 119:136 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕግህን አልጠበቅሁምና የውኃ ፈሳሽ ከዐይኖቼ ፈሰሰ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕግህ ባለመከበሩ፤ እንባዬ እንደ ውሃ ይፈስሳል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰዎች ሕግህን ስለ ጣሱ እንባዬ እንደ ወንዝ ውሃ ይፈስሳል።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 119:136
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት በግንባሩ ወድቆ እያለቀሰ በሚጸልይበትና በሚናዘዝበት ጊዜ፤ ወንዶች፥ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙበት እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፥ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ።


ቃልህን አልጠበቁምና ሰነፎችን አይቼ አዘንሁ።


ሕግህን ከተዉ ከኃጢአተኞች የተነሣ ኀዘን ያዘኝ።


ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የጌታም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ እጅግ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች።


ይህን ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና ፈጽሞ በማይሽር ቁስል ቆስላለችና ዐይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ።


ተወግተው ስለ ሞቱት ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን እንዳለቅስ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!


ዐይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ያነሳሱ።


ጌታም እንዲህ አለው፦ በከተማይቱ መካከል፥ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኩሰት ሁሉ በሚተክዙና በሚያለቅሱ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክትን አድርግ።


ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ እንዲህ እያለ አለቀሰላት፤


“እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና፥ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ።” ሳሙኤልም እጅግ ተቆጥቶ፥ ሌሊቱን ሁሉ ወደ ጌታ ጮኸ።