Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዕዝራ 10:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት በግንባሩ ወድቆ እያለቀሰ በሚጸልይበትና በሚናዘዝበት ጊዜ፤ ወንዶች፥ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙበት እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፥ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ወድቆ በሚጸልይበት፣ በሚናዘዝበትና በሚያለቅስበት ጊዜ ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች የሚገኙበት እጅግ ብዙ የእስራኤል ማኅበር በዙሪያው ተሰበሰበ፤ እነርሱም እንደዚሁ አምርረው አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዕዝራ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ለጸሎት ተንበርክኮ እያለቀሰ የተፈጸመውን ኃጢአት ሁሉ ለእግዚአብሔር በሚናዘዝበት ጊዜ ወንዶችም፥ ሴቶችም፥ ሕፃናትም ጭምር ያሉበት ቊጥሩ የበዛ የእስራኤል ማኅበር መጥቶ በዙሪያው በመሰብሰብ በመረረ ሁኔታ ያለቅሱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዕዝ​ራም እያ​ለ​ቀ​ሰና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​ወ​ደቀ በጸ​ለ​የና በተ​ና​ዘዘ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ የወ​ን​ድና የሴት፥ የሕ​ፃ​ና​ትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰበ፤ ሕዝ​ቡም እጅግ አለ​ቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዕዝራም እያለቀሰና በእግዚአብሔር ቤት ፊት እየወደቀ በጸለየና በተናዘዘ ጊዜ ከእስራኤል ዘንድ የወንድና የሴት የሕፃናትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፤ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕዝራ 10:1
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕግህን አልጠበቅሁምና የውኃ ፈሳሽ ከዐይኖቼ ፈሰሰ።


ታላቅ ኃዘን የማያቋርጥም ሥቃይ በልቤ አለ።


አገልጋይህና ሕዝብህ እስራኤል በዚህ ስፍራ የሚጸልዩትን ልመና ስማ፤ በማደሪያህ በሰማይ ስማን፤ ሰምተህም ይቅር በለን።


ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ እንዲህ እያለ አለቀሰላት፤


ገዢው ነህምያ፥ ጸሐፊው ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝቡን የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ፦ “ይህ ቀን ለጌታ አምላካችሁ ቅዱስ ነው፤ አታልቅሱ እንባም አታፍስሱ” አሉአቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና።


በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ማሉክ፥ ሐሪም፥ ባዓና።


‘ክፉ ነገር፥ ሰይፍ ወይም ፍርድ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን ስምህ ባለበት በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ ቆመን በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።’


እስራኤል ሆይ! በኃጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ተመለስ።


ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የጌታም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ እጅግ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች።


ተወግተው ስለ ሞቱት ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን እንዳለቅስ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!


ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም፥ መተላለፌን ለጌታ እነግራለሁ አልሁ፥ አንተም የኃጢአቴን ሸክም ተውህልኝ።


“በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ።


ጊዜውንም በፈጸምን ጊዜ ወጥተን ሄድን፤ ሁላቸውም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር እስከ ከተማው ውጭ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ጸለይን፤


ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለው “በዚች ሰዓት የዛሬ አራት ቀን የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት በቤቴ እጸልይ ነበር፤ እነሆም፥ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው በፊቴ ቆመና


የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ከሕፃናቶቻቸውና ከሚስቶቻቸው ከልጆቻቸውም ጋር በጌታ ፊት ቆመው ነበር።


ይሰሙና ጌታ አምላካችሁንም መፍራት ይማሩ ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ በጥንቃቄ እንዲከተሉ ሕዝቡን ይኸውም ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና በከተሞችህ የሚኖረውንም መጻተኛ ሰብስብ።


ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ ይጠመቁ ነበር።


ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሣ፥ ወደ ኤልያሺብ ልጅ ወደ ይሆሐናን ክፍል ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹ አለመታመን አዝኖ ነበርና በዚያ ገብቶ እንጀራ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም።


እነዚህን ቃላት በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ። ለብዙ ቀኖች አዘንሁ፤ በሰማይ አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥


እኔ አገልጋይህ ዛሬ በፊትህ ስለ አገልጋዮችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ለመስማት ጆሮህ ያድምጥ፥ ዐይኖችህም ይከፈቱ፥ በአንተ ላይ ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኃጢአት እናዘዛለሁ፤ እኔና የአባቴ ቤት ኃጢአት አድርገናል።


ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በጌታ ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።


ኢያሱም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ በሴቶቹም በሕፃናቱም በመካከላቸውም በሚኖሩት መጻተኞች ፊት ሙሴ ካዘዘው አንዲት ቃል እንኳ ሳያስቀር ሁሉን አነበበ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች