ክፉ ለማድረግ የሚያውጠነጥን፥ ተንኰለኛ ይባላል።
ክፋት የሚያውጠነጥን፣ “ተንኰለኛ” ይባላል።
ዘወትር ክፋትን ለማድረግ የሚያሤር ሁሉ “ተንኰለኛ” የሚል የቅጽል ስም ይወጣለታል፤
ነገር ግን በአንድነት ያስባሉ፥ ሰነፎችንም ድንገት ሞት ያገኛቸዋል።
በአባቴ በንጉሥ ዳዊት ላይ የፈጸምከውን በደል ሁሉ በደንብ ታውቃለህ፤ አንተ ስላደረግኸው ክፉ ነገር ጌታ ራሱ ይቀጣሃል፤
ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ።
ክፉ የሚያደርጉ ይስታሉ፥ ምሕረትና እውነት ግን መልካምን ለሚያደርጉ ናቸው።
ልባቸው ግፍን ታስባለችና፥ ከንፈራቸውም ተንኮልን ትናገራለችና።
የሞኝ እቅድ ኃጢአት መሥራት ነው። ሰዎች ፌዘኛውን ይጸየፉታል።
ጠማማነት በልቡ አለ፥ ሁልጊዜም ክፋትን ያቅዳል፥ ጠብንም ይዘራል።
ክፉ አሳብን የሚያቅድ ልብ፥ ወደ ክፉ የሚሮጡ እግሮች፥
የሸንጋይ ሽንገላ ክፉ ናት፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆንም እንኳን በሐሰት ቃል ድሀውን ለማጥፋት ክፉን አሳብ ያስባል።
በጌታ ላይ ክፉ ነገር የሚያሤር፥ ክፋትንም የሚመክር፥ ከአንቺ ዘንድ ወጥቶአል።
ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚዳፈሩ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚያውጠነጥኑ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥