ምሳሌ 22:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ዐይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፥ የአታላዩን ቃላት ግን ይገለብጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ የማይታመኑትን ሰዎች ቃል ግን እርሱ ከንቱ ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ እምነት የሌላቸውን ሰዎች ዕቅድ ግን ያስወግዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ ኃጥእ ግን የጥበብን ቃል ይንቃል። |
ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”
እንዲህም ሆነ፥ ጠላቶቻችን በእኛ ዘንድ እንደታወቀ፥ እግዚአብሔርም ምክራቸውን ከንቱ እንዳደረገው በሰሙ ጊዜ፥ እኛ ሁላችንም ወደ ቅጥሩ፥ እያንዳንዳችን ወደ ሥራችን ተመለስን።