ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፥ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ።
እንቅልፍ አትውደድ፤ አለዚያ ድኻ ትሆናለህ፤ ዐይንህን ክፈት፤ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖርሃል።
ጊዜህን በእንቅልፍ ብትጨርስ ትደኸያለህ፤ ተግተህ ብትሠራ ግን በቂ ምግብ ይኖርሃል።
እንዳትወገድ ማማትን አትውደድ። ድሃም እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ ዐይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ።
የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፥ የትጉ እጅ ግን ሀብታም ታደርጋለች።
መሬቱን የሚቆፍር ሰው እንጀራ ይጠግባል፥ ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን ማስተዋል የተሣነው ነው።
የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፥ አንዳችም አታገኝም፥ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።
ሥራ መፍታት እንቅልፍን ታመጣለች፥ የታካችም ነፍስ ትራባለች።
ዕቃ የሚገዛ “አይረባም አይረባም” ብሎ ያራክሳል፥ ገዝቶ ሲመለስ ግን በገዛው ዕቃ ይኩራራል።
ምድሩን የሚያርስ እንጀራ ይጠግባል፥ የማይረቡ ሰዎችን የሚከተል ግን ድህነት ይሞላበታል።
ገና ሳይነጋ ትነሣለች ለቤትዋም ሰዎች ምግባቸውን፥ ለአገልጋዮችዋም ሥራ ትሰጣለች።
የመርከቡ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “እንዴት ትተኛለህ? ተነሥ አምላክህን ጥራ፥ ምናልባትም እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን ይሆናል” አለው።
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ጌታን አገልግሉ፤
እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት ጊዜው አሁን መሆኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ አሁን መዳናችን ወደ እኛ ቀርቧልና።
ወደ ሰከነ ልቦናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና ይህንንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው።
የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ስለዚህ “አንተ የምታንቀላፋ ንቃ፤ ከሙታንም ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል፤” ተብሏል።
እንዲሁም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ማንም ሊሠራ የማይወድ አይብላ፤” ብለን አዘናችሁ ነበር።