Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 10:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፥ የትጉ እጅ ግን ሀብታም ታደርጋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሰነፍ እጆች ሰውን ያደኸያሉ፤ ትጉህ እጆች ግን ብልጽግናን ያመጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ስንፍና ያደኸያል፤ ተግቶ መሥራት ግን ያበለጽጋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የሐኬተኛ እጅ ችግረኛ ያደርጋል፤ የትጉህ እጅ ግን ባለጠጋ ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 10:4
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ግን ለመጉደል ይቸኩላል።


ታካች ሰው በብርድ ምክንያት አያርስም፥ ስለዚህ በመከር ይለምናል፥ ምንም አያገኝም።


ሥራ መፍታት እንቅልፍን ታመጣለች፥ የታካችም ነፍስ ትራባለች።


የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፥ አንዳችም አታገኝም፥ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።


ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።


ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፥ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ።


ታካች ሰው እጁን በወጭቱ ያጠልቃታል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።


የትጉ እጅ ትገዛለች፥ የታካች እጅ ግን ትገብራለች።


በልግስና የሚሰጥ ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፥ ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም።


ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”


ተግባር በመፍታት ጣራው ይዘብጣል፥ በእጅም መታከት ቤት ያፈስሳል።


በበጋ የሚያከማች ልጅ አስተዋይ ነው፥ በመከር የሚተኛ ግን እርሱ ራሱን ያስነውራል።


ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፥ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።


በሥራው ታካች የሚሆን የሀብት አጥፊ ወንድም ነው።


በዚያም ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጡ፥ ስለ ቈፈሩአትም ጉድጓድ፦ “ውኃ አገኘን ብለው ነገሩት።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች