ምሳሌ 15:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአዋቂ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፥ የሰነፎች አፍ ግን በስንፍና ይሰማራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይሻል፤ የሞኝ አፍ ግን ቂልነትን ያመነዥካል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ አእምሮ ያለው ሰው ዕውቀትን ይፈልጋል፤ ሞኞች ግን በድንቊርናቸው ይረካሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀና ልብ ዕውቀትን ትፈልጋለች። የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል። |
እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና “ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን?” ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።