ኢሳይያስ 30:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ባለ ራእዮችን፦ “አትመልከቱ” ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ “ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ባለራእዮችን፣ “ከእንግዲህ ራእይን አትዩ!” ይላሉ፤ ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፤ “እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን፤ ደስ የሚያሠኘውን ንገሩን፤ የሚያማልለውን ተንብዩልን። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ነቢያትንም አፋቸውን ለማስያዝ እንዲህ ይሉአቸዋል፦ ‘ቀጥተኛ የሆነውን ነገር አትንገሩን፤ እኛ ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ንገሩን፤ ለስላሳና ማረሳሻ የሆነውን ነገር አስተምሩን። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ነቢያትን፥ “አትንገሩን፤ ባለ ራእዮችንም አታውሩን፤ ነገር ግን ሌላውን ስሕተት አስረዱን፤ ንገሩንም” ይላሉ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ባለ ራእዮችን፦ አትመልከቱ ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፥ ምዕራፉን ተመልከት |