Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 15:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ልቡ የሚያዝን ሰው ዘመኑ ሁሉ የከፋች ናት፥ የልብ ደስታ ግን ሁልጊዜ እንደ ግብዣ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የተጨቈኑ ሰዎች ዘመናቸው ሁሉ የከፋ ነው፤ በደስታ የተሞላ ልብ ግን የማይቋረጥ ፈንጠዝያ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የጭቊን ኑሮ ዘወትር ጐስቋላ ነው፤ ደስተኞች ሰዎች ግን ዘወትር በኑሮአቸው ይረካሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የክፉዎች ዐይኖች ሁልጊዜ ክፋትን ይመለከታሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን ሁልጊዜ ዝም ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 15:15
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ።


ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ “የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፥ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”


ደስ ያለው ልብ ፊትን ያበራል፥ በልብ ኀዘን ግን ነፍስ ትሰበራለች።


የአዋቂ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፥ የሰነፎች አፍ ግን በስንፍና ይሰማራል።


ጌታን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ሁከት ካለበት ከብዙ መዝገብ ይሻላል።


ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፥ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው።


ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፥ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች።


በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፤ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር


በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤


ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።


ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።


የክርስቶስ ሥቃይ ስለ እኛ እንደ መብዛቱ፥ መጽናናታችንም በክርስቶስ በኩል ይበዛልናል።


ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድኾች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።


ይልቅስ የእርሱ ክብር በሚገለጥበት ጊዜ ደግሞ ደስ ብሎአችሁ ኀሤት እንድታደርጉ የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በሆናችሁበት መጠን ደስ ይበላችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች