ምሳሌ 12:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውን የልቡ ኀዘን ያዋርደዋል፥ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጉ ልብ ሰውን በሐዘን ይወጥራል፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሠኘዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሐሳብ መጨነቅ ሐዘንን ያመጣል፤ በጎ ንግግር ግን ያስደስታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያስደነግጥ ቃል የጻድቅ ሰው ልቡናን ያውካል፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል። |
የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።