Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 15:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የዐይን ብርሃን ልብን ደስ ያሰኛል፥ መልካም ወሬም አጥንትን ያለመልማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ብሩህ ገጽታ ልብን ደስ ያሰኛል፤ መልካም ዜናም ዐጥንትን ያለመልማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 በፈገግታ የተሞላ ፊት ልብን ያስደስታል፤ የምሥራች ቃልም አጥንትን ያለመልማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 መልካምን ነገር የሚያይ ዐይን ልብን ደስ ያሰኛል፥ መልካም ዜናም አጥንትን ያለመልማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 15:30
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።


የቀዘቀዘ ውኃ ለደረቀ ጉሮሮ ደስ እንደሚያሰኝ፥ ከሩቅ አገር የመጣ መልካም ምሥራች እንዲሁ ነው።


ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።


ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት፥ መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።


ብርሃን ጣፋጭ ነው ፀሐይንም ማየት ለዐይን መልካም ነው።


ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፥ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች።


ሁልጊዜ ለጻድቃን ብርሃን ነው፥ የኀጥኣን መብራት ግን ይጠፋል።


የዙፋንህ መሠረት ጽድቅና ፍርድ፥ ምሕረትና እውነት በፊትህ ይሄዳሉ።


አሁንም ትሩፋን እንዲያስቀርልን፥ በተቀደሰውም ስፍራው ችንካርን እንዲሰጠን፥ አምላካችንም ዓይናችንን እንዲያበራ፥ በባርነትም ሳለን ጥቂት የሕይወት መታደስን እንዲሰጠን ለጥቂት ጊዜ ከጌታ ከአምላካችን ሞገስ ተሰጥቶናል።


ይህም ለሥጋህ ፈውስ ይሆንልሃል፥ ለአጥንትህም መታደስ።


ጌታ ከኀጥኣን ይርቃል፥ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።


የሕይወትን ተግሣጽ የሚሰማ ጆሮ በጠቢባን መካከል ይኖራል።


ሰውን የልቡ ኀዘን ያዋርደዋል፥ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች