ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።
ምሳሌ 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ሐብል ይሆንልሃልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለራስህ ሞገስን የሚያጐናጽፍ አክሊል፣ ዐንገትህን የሚያስውብ ድሪ ይሆንልሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ለራስህ ክብርን እንደሚያቀዳጅ ዘውድ፥ ለአንገትህም ውበትን እንደሚሰጥ ሐብል ይሆኑልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለራስህ የክብር ዘውድን ለአንገትህም የወርቅ ድሪ ታገኛለህና። |
ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።
እኛም የአባታችንን የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብን ቃል ሰምተን፥ ባዘዘን ነገር ሁሉ ታዝዘናል፤ እኛም ሚስቶቻችንም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም ዕድሜአችንን ሙሉ የወይን ጠጅ አልጠጣንም፤