ምሳሌ 1:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግርግር ባለበት አደባባይ ትጣራለች፥ በከተማይቱ መግቢያ በር ቃልን ትናገራለች፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዉካታ በበዛባቸው ጐዳናዎች ላይ ትጮኻለች፤ በከተማዪቱም መግቢያ በር ላይ እንዲህ ትላለች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው በሚበዛበት መንገድ ትጮኻለች፤ በከተማው መግቢያ የሕዝብ መሰብሰቢያ ላይ ንግግርዋን ታሰማለች። እንዲህም ትላለች፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግንብ ድምድማት ትሰብካለች፥ በኀያላን በሮች ታገለግላለች። በከተማ በሮች በድፍረት እንዲህ ትላለች፦ |
ኢየሱስም መልሶ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።