Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 18:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ኢየሱስም መልሶ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለዓለም በግልጽ ተናግሬአለሁ፤ አይሁድ በተሰበሰቡበት ምኵራብ፣ በቤተ መቅደስም ሁልጊዜ አስተምሬአለሁ፤ በስውር የተናገርሁት የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለሰው ሁሉ በግልጥ ተናገርኩ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኲራብም ሆነ በቤተ መቅደስ፥ ዘወትር አስተማርኩ፤ በስውር የተናገርኩት ምንም ነገር የለም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ ለዓ​ለም በግ​ልጥ ተና​ገ​ርሁ፤ አይ​ሁድ ሁሉ በሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት በም​ኵ​ራ​ብም፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ሁል​ጊዜ አስ​ተ​ማ​ርሁ፤ በስ​ው​ርም የተ​ና​ገ​ር​ሁት አን​ዳች ነገር የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ኢየስስም መልሶ፦ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ እኔ ሁልጊዜ አስተማርሁ፥ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 18:20
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከአንበሳ አፍ አድነኝ፥ ከጐሽ ቀንድም ጠብቀኝ፥ መለስክልኝ!


አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”


በስውር ወይም በጨለማ ምድር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፤ እኔ ጌታ እውነትን እናገራለሁ ትክክለኛውንም አወራለሁ።


ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርኩም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርኩ፥ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።


ስለዚህ ‘እነሆ በበረሀ አለ’ ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ ‘እነሆ በቤት ውስጥ ነው’ ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤


በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው “ወንበዴን እንደምትይዙ እኔን ለመያዝ ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ ወጣችሁን? ዕለት በዕለት በመቅደስ ተቀምጬ ሳስተምር ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህኑ ልብሱን ቀደደና እንዲህ አለ “ተሳድቦአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን መያዝ ለምን ያስፈልገናል? እነሆ አሁን ስድቡን ሰምታችኋል፤


ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትን ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝቡ መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።


ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሽታንና ሕማምን ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተሞችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።


እርሱም ይህን በግልጽ ነገራቸው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው ወስዶ ይገሥጸው ጀመር።


ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፤ ሌሊት ግን ደብረዘይት ወደምትባል ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር።


እንዲሁም በሁሉም እየተመሰገነ በምኵራባቸው ያስተምር ነበር።


ስለምን እኔን ትጠይቀኛለህ? ስናገር የሰሙኝን ጠይቅ፤ እነሆ፥ እነርሱ እኔ የተናገርሁትን ያውቃሉ፤” አለው።


በቅፍርናሆም፥ በምኵራብ ሲያስተምር ነበር ይህን ያለው።


በበዓሉ እኩሌታ ኢየሱስ ወደ መቅደስ ወጥቶ ያስተምር ነበር።


እነሆ፥ በግልጥ ይናገራል፤ ነገር ግን ምንም አይሉትም። አለቆቹ ይህ ሰው ክርስቶስ እንደሆነ በእውነት አወቁን?


እንግዲህ ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር “እኔንም ታውቁኛላችሁ፤ ከወዴትም እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው፤


በይፋ መታወቅ እየፈለገ በስውር የሚሠራ የለምና። እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ እራስህን ለዓለም ግለጥ፤” አሉት።


ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር።


ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ፤” አላቸው።


በእርሱ ፊት ደግሞ በግልጥ የምናገረው ንጉሥ ይህን ነገር ያውቃል፤ ከዚህ ነገር አንዳች እንዳይሰወርበት ተረድቼአለሁና፤ ይህ በስውር የተደረገ አይደለምና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች