ከምርኮ የተመለሱት የእስራኤል ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ራሳቸውን ከምድር አሕዛብ ርኩሰት ለይተው ወደ እነርሱ መጥተው የነበሩት ሁሉ በሉት።
ዘኍል 9:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመካከላችሁም መጻተኛ ቢኖር፥ ለጌታም የፋሲካን በዓል ቢያከብር፥ እንደ ፋሲካ ሥርዓትና እንደ ደንቡ እንዲሁ ያክብር፤ ለመጻተኛና ለአገሩ ተወላጅ አንድ ዓይነት ሥርዓት ይኑራችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማክበር ቢፈልግ በሕጉና በሥርዐቱ መሠረት መፈጸም አለበት፤ ለመጻተኛውም ሆነ ለአገሬው ተወላጅ የሚኖራችሁ ሕግ አንድ ይሁን።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእናንተ መካከል መጻተኛ የእግዚአብሔርን ፋሲካ በዓል ለማክበር ቢፈልግ በተወሰነው ደንብና የሥርዓት መመሪያ ሁሉ መሠረት ማክበር ይኖርበታል፤ የአገር ተወላጁም ሆነ መጻተኛ ይህን ደንብ በተመሳሳይ ሁኔታ ይፈጽም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አገራችሁ መጻተኛ ቢመጣ፥ የእግዚአብሔርን ፋሲካ እንደ ፋሲካው ሕግ እንደ ትእዛዙም ያድርግ፤ ለመጻተኛና ለሀገር ልጅ አንድ ሥርዐት ይሁንላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመካከላችሁም መጻተኛ ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያደርግ ዘንድ ቢወድድ፥ እንደ ፋሲካ ሥርዓት እንደ ፍርዱም እንዲሁ ያድርግ፤ ለመጻተኛና ለአገር ልጅ አንድ ሥርዓት ይሁንላችሁ። |
ከምርኮ የተመለሱት የእስራኤል ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ራሳቸውን ከምድር አሕዛብ ርኩሰት ለይተው ወደ እነርሱ መጥተው የነበሩት ሁሉ በሉት።
ከእንግዳም ሰው እጅ የተገኙ እንደነዚህ ያሉ እንስሶችን ሁሉ ለአምላካችሁ እንጀራ እንዲሆኑ አታቅርቡ፤ ርኩሰትም ነውርም አለባቸውና አይሠምሩላችሁም።”
ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ ለጉባኤው ሁሉ አንድ ዓይነት ሥርዓት ይኑር፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁት መጻተኛውም በጌታ ፊት እንዲሁ ይሆናል።
ይሰሙና ጌታ አምላካችሁንም መፍራት ይማሩ ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ በጥንቃቄ እንዲከተሉ ሕዝቡን ይኸውም ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና በከተሞችህ የሚኖረውንም መጻተኛ ሰብስብ።