Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 19:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሀውና ለእንግዳው ተወው፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የወይንህን ዕርሻ አትቃርም፤ የወደቀውንም አትልቀም፤ ለድኾችና ለመጻተኞች ተውላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የወይን መከርህንም ስትሰበስብ በሐረጉ ላይ ተሰውሮ የቀረውን ወይም በመሬት ላይ የረገፈውን የወይን ዘለላ አጥርተህ ለመልቀም እንደገና ወደ ኋላ አትመለስ፤ ይህን ሁሉ ለድኾችና ለመጻተኞች ተውላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የወ​ይ​ን​ህን ቃር​ሚያ አጥ​ር​ተህ አት​ቃ​ርም፤ የወ​ደ​ቀ​ው​ንም የወ​ይ​ን​ህን ፍሬ አት​ሰ​ብ​ስብ፤ ለድ​ሆ​ችና ለእ​ን​ግ​ዶች ተወው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 19:10
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የወይራ ዛፍ ሲያራግፉት በቅርንጫፉ ራስ ላይ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ እንደሚቀር፥ አራት ወይም አምስት ፍሬ ችፍግ ባለው ቅርንጫፍ ላይ እንደሚገኝ፥ እንዲሁ ጥቂት ቃርሚያ ይቀራል፥ ይላል ጌታ የእስራኤል አምላክ።


የወይራን ዛፍ እንደ መምታት፥ ከወይንም መከር በኋላ ቃርሚያውን እንደ መልቀም፥ እንዲሁ በምድርና በአሕዛብም መካከል ይሆናል።


ወይን ለቃሚዎች ቢመጡብህ፥ ቃርሚያውን አይተዉልህምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፥ የሚዘርፉት የሚበቃቸውን ያህል አይደለምን?


እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና፤ ስለዚህ ራሳችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤ በምድርም ላይ በደረታቸው እየተሳቡ በሚርመሰመሱ ሁሉ የገዛ አካላችሁን አታርክሱ።


“አትስረቁ፥ አትካዱም፥ ከእናንተም ማንም ሰው ወንድሙን አያታልል።


የተትረፈረፈም ፍሬ አብዝተው እንዲሰጡዋችሁ የአምስተኛውን ዓመት ፍሬ ብሉ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


“የምድራችሁንም መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ እስከ እርሻችሁ ድንበር ድረስ ፈጽማችሁ አትሰብስቡ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ።


“የምድራችሁንም መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ እስከ እርሻችሁ ድንበር ድረስ ፈጽማችሁ አትሰብስቡ። የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ፤ ለድሀውና ለእንግዳው ተዉት። እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”


የምድሪቱ ሰንበት ለእናንተ፥ ለአንተም፥ ለወንድ ባርያህም፥ ለሴት ባርያህም፥ ተቀጥሮ ለሚያገለግልህም፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ለመጻተኛም ምግብ ትሰጣችኋለች።


ሌቦች ቢመጡብህ ወይም ወንበዴዎች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን ብቻ ይሰርቁ የለምን? ወይንንም የሚቆርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ ያስቀሩ የለምን? አንተ ግን ምንኛ ጠፋህ!


የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።


“የዕርሻህን ሰብል በምታጭድበት ጊዜ፥ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሰህ አትሂድ። ጌታ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።


የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።


የወይን ተክልህን ፍሬ ስትሰበስብ ቃርሚያውን ለመሰብሰብ አትመለስበት፤ የቀረውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።


ጌዴዎን ግን፥ “እናንተ ካደረጋችሁት ጋር ሲነጻጸር የእኔ ከምን ይቈጠራል? የኤፍሬም የወይን ቃርሚያ ተጠቃሎ ከገባው ከአቢዔዝር የወይን መከር አይበልጥምን?


ሞአባዊቱም ሩት ናዖሚንን፦ “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው ተከትዬ እህል ለመቃረም ወደ እርሻ ልሂድ” አለቻት። እርሷም፦ “ልጄ ሆይ፥ ሂጂ” አለቻት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች