ዘኍል 6:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም እነዚህን ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ ይህም ከሚወዘወዘው ፍርምባና ከሚቀርበው ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻው ነው። ከዚያም በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ካህኑ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ እነዚህም የተቀደሱ ናቸው። ከተወዘወዘው ፍርምባና ከቀረበው ወርች ጋራ የተቀደሱ የካህኑ ድርሻ ይሆናሉ። ከዚህ በኋላ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት ይችላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ካህኑ ይህን ሁሉ ወስዶ ለእግዚአብሔር የሚወዘወዝ ልዩ መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤ ይህም ሁሉ የካህኑ ድርሻ ሆኖ ከሚነሣው ከአውራው በግ ፍርንባና ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት የሚፈቀድለትም ከዚያን በኋላ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም እነዚህን ሁሉ ቍርባን አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል፤ ይህም የቍርባን ፍርምባና የመባው ወርች ለካህኑ የተቀደሰ ነው፤ ከዚያም በኋላ ባለስእለቱ ወይን ይጠጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም እነዚህን ለመወዝወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ ይህም ከሚወዘወዘው ፍርምባና ከሚነሣው ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ነው። ከዚያም በኋላ ናዝራዊው ወይን ይጠጣ ዘንድ ይችላል። |
የሠራዊት ጌታም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ መልካምና የበሰለ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።
ጌታም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፥ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላላም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
የሚነሣውን ወርች የሚወዘወዘውንም ፍርምባ፥ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ከሆነው ስብ ጋር ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት እንዲወዘወዝ ያመጣሉ፤ ጌታ እንዳዘዘ ለአንተ ከአንተ ጋርም ላሉት ለልጆችህ የዘለዓለም ድርሻ ይሆናል።”
የእርሱ እጆች ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያመጣሉ፤ እርሱም ፍርምባው በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን እንዲወዘወዝ ፍርምባውን ከስቡ ጋር ያመጣዋል።
የሚወዘወዘውን ፍርምባና እንደ ቁርባን የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕታቸው ወስጄ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ድርሻ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ እነርሱን ሰጥቼአቸዋለሁ።
የኤፍሬምም ሰዎች እንደ ኃያላን ይሆናሉ፥ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ደስ ይለዋል፤ ልጆቻቸውም አይተው ደስ ይላቸዋል፥ ልባቸውም በጌታ ሐሤት ያደርጋል።
የሠራዊት ጌታ ይጠብቃቸዋል፤ እነርሱም ይውጧቸዋል፥ በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ፤ ይጠጧቸዋል፥ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይሞቃቸዋል፤ እንደ መሠዊያም ማዕዘኖች፥ እንደ ጥዋዎቹም የተሞሉ ይሆናሉ።
“ስእለቱን የተሳለው የናዝራዊ፥ የመግዛት አቅሙ ከሚፈቅድለት ሌላ ስለ ናዝራዊነቱ ለጌታ የሚያቀርበው የቁርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ናዝራዊነቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል።”