ዘኍል 6:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 “ስእለቱን የተሳለው የናዝራዊ፥ የመግዛት አቅሙ ከሚፈቅድለት ሌላ ስለ ናዝራዊነቱ ለጌታ የሚያቀርበው የቁርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ናዝራዊነቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 “ ‘ስእለቱን ለመፈጸም ለእግዚአብሔር ለሚሳል ናዝራዊ ሕጉ ይኸው ነው፤ ሊቀርብ ከሚችለው በላይ ለእግዚአብሔር ለመስጠት ቃል ለሚገባው ነገር እንደ ናዝራዊነቱ በተሳለው መሠረት መሆን አለበት። በናዝራዊነት ሕግ መሠረት የተሳለውን ስእለት መፈጸም ይገባዋል።’ ” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 “እንግዲህ እነዚህ ስለ ናዝራውያን የተሰጡ የሕግ መመሪያዎች ናቸው፤ ነገር ግን አንድ ናዝራዊ በስእለቱ መሠረት ሊያቀርብ ከሚገባው በላይ ለመስጠት ቃል ቢገባ በገባው ቃል መሠረት ስእለቱን መፈጸም አለበት።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 “ስእለቱን የተሳለው የባለስእለቱ፥ እጁም ከሚያገኘው ሌላ ስለ ስእለቱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የቍርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ስእለቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ስእለቱን የተሳለው የናዝራዊ፥ እጁም ከሚያገኘው ሌላ ስለ ናዝራዊነቱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የቍርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ናዝራዊነቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል። ምዕራፉን ተመልከት |