ዘሌዋውያን 10:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የሚነሣውን ወርች የሚወዘወዘውንም ፍርምባ፥ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ከሆነው ስብ ጋር ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት እንዲወዘወዝ ያመጣሉ፤ ጌታ እንዳዘዘ ለአንተ ከአንተ ጋርም ላሉት ለልጆችህ የዘለዓለም ድርሻ ይሆናል።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 የቀረበውን ወርችና የተወዘወዘውን ፍርምባ በእግዚአብሔር ፊት የመወዝወዝ መሥዋዕት ሆኖ በእሳት ከቀረበው ሥብ ጋራ ይምጣ። ይህም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም የተመደበ ድርሻ ይሆናል።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ስቡ ለእግዚአብሔር የምግብ መባ ሆኖ በሚቀርብበት ጊዜ ወርቹንና ፍርምባውን ያመጣሉ፤ ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም የተመደበ ድርሻ ይሆናል።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የመሥዋዕቱን ወርችና ፍርምባ በእግዚአብሔር ፊት ከሚቀርበው መሥዋዕት የእሳት ቍርባን ከሆነው ስብ ጋር ያመጣሉ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ለአንተ፥ ከአንተ ጋርም ለወንዶችና ሴቶች ልጆችህ የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የሚነሣውን ወርች የሚወዘወዘውንም ፍርምባ በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን እንዲወዘውዙ የእሳት ቍርባን ከሆነው ስብ ጋር ያመጣሉ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ለአንተ ከአንተ ጋርም ለልጆችህ የዘላለም ሥርዓት ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከት |