ኢሳይያስ 25:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 የሠራዊት ጌታም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ መልካምና የበሰለ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣ ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣ የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣ ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝቡ ሁሉ ግብዣን ያደርጋል፤ በዚህ ተራራ ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ፤ የወይን ጠጅንም ይጠጣሉ፤ ዘይትንም ይቀባሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል። ምዕራፉን ተመልከት |