ሳዶቅም በዚያ ነበር፤ አብረውት የነበሩትም ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው መጡ፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት፥ ሕዝቡ በሙሉ ከከተማዪቱ ለቆ እስኪ ወጣ ድረስ፥ አብያታር አጠገብ አስቀመጡ።
ዘኍል 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃዎች ሁሉ መሸፈናቸውን በጨረሱ ጊዜ፥ ሰፈሩም ለመጓዝ ሲነሣ፥ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ከዚያም በኋላ ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። የቀዓት ልጆች የሚሸከሙአቸው የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና ዕቃዎቹን፣ ንዋየ ቅድሳቱንም በሙሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ሲሆን፣ ቀዓታውያን ለመሸከም ይምጡ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን መንካት የለባቸውም፤ ስለዚህ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያሉትን እነዚህን ዕቃዎች የሚሸከሙ ቀዓታውያን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይገባሉ። እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በምስክሩ ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰፈሩም ሲነሡ፥ አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በመገናኛው ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው። |
ሳዶቅም በዚያ ነበር፤ አብረውት የነበሩትም ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው መጡ፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት፥ ሕዝቡ በሙሉ ከከተማዪቱ ለቆ እስኪ ወጣ ድረስ፥ አብያታር አጠገብ አስቀመጡ።
በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙ፥ ለዘለዓለሙም እንዲያገለግሉት ጌታ ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የጌታን ታቦት ሊሸከም አይገባውም።”
ለሕዝቡም በዙሪያው ወሰን አድርግላቸው፥ እንዲህም በላቸው ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ጫፉንም እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ተራራውን የነካ ፈጽሞ ይሞታል፤
ነገር ግን በምስክሩ ማደሪያና በዕቃው ሁሉ የእርሱም በሆነው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን ሹማቸው። ማደሪያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ይሸከሙ፥ ያገልግሉትም፥ በማደሪያውም ዙሪያ ይስፈሩ።
እነርሱም ትእዛዝህን የድንኳኑንም ሁሉ አገልግሎት ግዴታ ይፈጽሙ፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ፥ እናንተም ደግሞ ከእነርሱ ጋር እንዳትሞቱ፥ እነርሱ ወደ መቅደሱ ዕቃና ወደ መሠዊያው አይቅረቡ።
በማደሪያውም ፊት በምሥራቅ በኩል በመገናኛው ድንኳን ፊት በስተ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት ሙሴና አሮን ልጆቹም ይሆናሉ፥ በመቅደሱም ውስጥ ማናቸውንም ለእስራኤል ልጆች የሚደረገውን ሥርዓት ይጠብቃሉ፤ ማናቸውም ልዩ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።
በእርሱም ላይ የሚገለገሉባቸውን የመሠውያውን ዕቃዎች ሁሉ፥ ጀሞዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ጐድጓዳ ሳሕኖቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም ላይ የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።
ነገር ግን እጅግ ቅዱስ ወደ ሆኑት ነገሮች በቀረቡ ጊዜ በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ እንዳይሞቱ እንዲህ አድርጉላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ይግቡ፥ እያንዳንዱንም ሰው በየተግባሩና በየሥራው ጫና ይመድቡት፤
ሙሴም ኢያሱን እንዳዘዘው ሁሉ፥ ጌታ ኢያሱን ለሕዝቡ እንዲነግር ያዘዘው ነገር ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ነበርና፤ ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ።
ጌታም ከቤትሼሜሽ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ምክንያቱም ወደ ጌታ ታቦት ውስጥ በመመልከታቸው ነበር። ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ ጌታ እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሱ።