Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 19:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ለሕዝቡም በዙሪያው ወሰን አድርግላቸው፥ እንዲህም በላቸው ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ጫፉንም እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ተራራውን የነካ ፈጽሞ ይሞታል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በተራራው ዙሪያ ለሕዝቡ ወሰን አበጅተህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ወይም ግርጌውን እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ማንም ተራራውን ቢነካ በርግጥ ይሞታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በተራራው ዙሪያ ድንበር አብጅ፤ እነርሱም ያንን ድንበር አልፈው ወደ ተራራው እንዳይወጡና እንዲያውም ድንበሩን እንዳይነኩ ንገራቸው፤ ማንም ሰው ከተወሰነው ድንበር አልፎ፥ ተራራውን ቢነካ በሞት ይቀጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ለሕ​ዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ወሰን አድ​ር​ግ​ላ​ቸው፤ ወደ ተራ​ራው እን​ዳ​ት​ወጡ፥ ከእ​ርሱ ማን​ኛ​ው​ንም ክፍል እን​ዳ​ት​ነኩ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ተራ​ራ​ው​ንም የነካ ፈጽሞ ይሞ​ታል” ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ወሰንም ለሕዝቡ በዙሪያው አድርግላቸው፦ ወደ ተራራው እንዳትወጡ ጫፉንም እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ተራራውንም የነካ ፈጽሞ ይሞታል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 19:12
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈርዖንም፦ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ ተጠንቀቅ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና ፊቴን እንዳታይ” አለው።


ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ውረድ፥ ጌታን ለማየት ዳርቻውን እንዳያልፉና ከእነርሱም ብዙዎቹ እንዳይጠፉ ሕዝቡን አስጠንቅቃቸው፤


ሙሴም ጌታን፦ “አንተ በተራራው ዙሪያ ወሰን አድርግ፥ ቀድሰውም ብለህ አስጠንቅቀኸናልና ሕዝቡ ወደ ተራራ ሊወጡ አይችሉም” አለው።


ሙሴም ብቻውን ወደ ጌታ ይቅረብ፤ እነርሱ ግን አይቅረቡ፥ ሕዝቡም ከእርሱ ጋር አይውጡ።”


በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትገባባት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤


ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይውጣ፥ በተራራውም ሁሉ ማንም አይታይ፤ መንጎችና ከብቶችም በዚያ ተራራ ፊት አይሰማሩ።”


ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች አገር ታልፋላችሁ፥ እነርሱም ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ።


“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።


ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፥ ወደ ጭጋጉና ወደ ጨለማው፥ ወደ ዐውሎ ነፋሱ ገና አልደረሳችሁም፤


በዚህ መንገድ በፊት አላለፋችሁበትምና የምትሄዱበትን መንገድ ታውቃላችሁ። በእናንተና በታቦቱ መካከል ግን ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ርቀት ይኑር፤ ወደ ታቦቱ አትቅረቡ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች