ዘፀአት 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የማንም እጅ አይንካው፤ የሚነካው ግን በድንጋይ ይወገራል፥ ወይም በፍላጻ ይወጋል፤ እንስሳም ቢሆን፥ ሰውም ቢሆን አይድንም።’ ሳያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በዚያን ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 በድንጋይ ይወገራል ወይም በቀስት ይወጋል፤ ምንም እጅ በርሱ ላይ አያርፍም፤ ሰውም ሆነ እንስሳ በሕይወት እንዲኖር አይተውም።’ ወደ ተራራው መውጣት የሚችሉት ከፍ ባለ ድምፅ መለከት በተነፋ ጊዜ ብቻ ነው።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ይኸውም ማንም ሳይነካው በድንጋይ ተወግሮ ወይም በፍላጻ ተወግቶ ይገደል፤ ይህን የሚያደርጉ ሰዎችም ሆኑ እንስሶች በዚሁ ዐይነት ይገደሉ፤ ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት የሚገባው ለረጅም ጊዜ መለከት ሲነፋ ብቻ ነው።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የማንም እጅ አይንካ፤ የሚነካውም ሁሉ በድንጋይ ይወገራል፤ ወይም በፍላጻ ይወጋል፤ እንስሳ ወይም ሰው ቢሆን የቀረበ አይድንም። የመለከት ድምፅና ደመና በተራራው በዐለፈ ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የማንም እጅ አይንካ፤ ነገር ግን የሚነካው ሁሉ ይወገራል፥ ወይም በፍላጻ ይወጋል፤ እንስሳ ወይም ሰው ቢሆን አይድንም በላቸው። ሳያቍርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በዚያን ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ። ምዕራፉን ተመልከት |