እኩለ ቀን ካለፈም በኋላ የሠርክ መሥዋዕት እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ እየተራወጡ ይቀባጥሩ ነበር፤ ይሁን እንጂ ምንም መልስ አላገኙም፤ ድምፅም አልተሰማም።
ዘኍል 28:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱን ጠቦት በማለዳ፥ ሌላውንም ጠቦት በማታ አቅርብ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዱን ጠቦት በማለዳ ሌላውን ደግሞ ማታ አቅርቡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው ጠቦት ጠዋት፥ ሁለተኛውም ጠቦት ማታ እንዲቀርብ አድርጉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱን ጠቦት በማለዳ፥ ሌላውንም ጠቦት በማታ አቅርቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱን ጠቦት በማለዳ፥ ሌላውንም ጠቦት በማታ አቅርብ፤ |
እኩለ ቀን ካለፈም በኋላ የሠርክ መሥዋዕት እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ እየተራወጡ ይቀባጥሩ ነበር፤ ይሁን እንጂ ምንም መልስ አላገኙም፤ ድምፅም አልተሰማም።
ከቀትር በኋላ የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ነቢዩ ኤልያስ ወደ መሠዊያው ቀርቦ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ጌታ ሆይ! አንተ የእስራኤል አምላክ መሆንክን፥ እኔም የአንተ አገልጋይ መሆኔን፥ እኔም ይህን ሁሉ ያደረግኹት በቃልህ መሠረት መሆኑን አንተ ራስህ ግለጥ፤
በዚያም ለእስራኤልም ባዘዘው በጌታ ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁልጊዜ ጥዋትና ማታ ለጌታ ያቀርባሉ።
የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ።
እንዲህም በላቸው፦ ‘ለጌታ በእሳት የምታቀርቡት ቁርባን ይህ ነው፤ ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ።
የኢንም መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቁርባን ታቀርባለህ።