ኢዩኤል 1:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤ እናንተ በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤ የእህል ቍርባኑና የመጠጥ ቍርባኑ፣ ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ለአምላካችሁ የምታቀርቡት የእህልም ሆነ የወይን ጠጅ መባ ስለሌለ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች የሆናችሁ ካህናት! ኑና ማቅ ለብሳችሁ ሌሊቱን ሁሉ አልቅሱ! እናንተም በመሠዊያው ላይ የምታገለግሉ ዋይ! ዋይ! በሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 መሥዋዕቱና የመጠጡ ቍርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት! ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የመሠውያ አገልጋዮች! ዋይ በሉ፤ እናንተም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የእህሉ ቍርባንና የመጠጡ ቍርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዬች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ። ምዕራፉን ተመልከት |