Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 12:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በዚህም ወር እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ወሩ በገባ እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቋቸው። በዚያ ምሽት ጀምበር ስትጠልቅ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይረዷቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እነዚህንም እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ጠብቁአቸው። በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ የእስራኤል ኅብረተሰብ ሁሉ እንስሶቹን ይረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በዚ​ህም ወር እስከ ዐሥራ አራ​ተኛ ቀን ድረስ ጠብ​ቁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሲመሽ ይረ​ዱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 12:6
34 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመጀመሪያው ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ሲመሽ የጌታ ፋሲካ ነው።


“በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን የጌታ ፋሲካ ነው።


በዓሉንም በሁለተኛው ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ ያክብሩ፤ እርሾ ካልገባበት ቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት።


በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን ምሽት እስከ ከወሩ ሀያ አንድ ቀን ምሽት ድረስ ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ።


በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።


በመጀመሪውያ ወር ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ። እስከ ሰባት ቀን ድረስ እርሾ ያልነካው ቂጣ ትበላላችሁ።


የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረማቸውን ሰማሁ፦ እንዲህ በላቸው “ወደ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፥ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።”


ሁሉም በአንድነት “ይህን አስወግደው፤ በርባንንም ፍታልን፤” እያሉ ጮኹ፤


የተሰበሰቡት በሙሉ ተነሥተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱትና


በሰቀሉትም ጊዜ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ነበረ።


የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ምትክ እንዲፈታላቸው እንዲጠይቁ ሕዝቡን አነሣሡ።


ሕዝቡም መጥተው እንደተለመደው እንዲያደርግላቸው ጲላጦስን ለመኑት።


ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፥ ከጸሓፍትና ከመላው የሸንጎ አባላት ጋር ወዲያው ከተማከሩ በኋላ ኢየሱስን አስረው ወሰዱት፤ ለጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።


ሕዝቡም ሁሉ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” ብለው መለሱ።


ሊቃነ ካህናቱና ሽማግሌዎቹ ግን በርባን እንዲለቀቅ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፋ ሕዝቡን አግባቡ።


በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል፤ በእርሱም የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።


እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፤


እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዐመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።


እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ ጌታም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።


ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ በዓል አድርጋችሁ ጠብቁት፥ ለጌታ በዓል ነው፤ ለትውልዳችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁታላችሁ።


በዚህም ቀን ሠራዊታችሁን ከግብጽ ምድር አውጥቼአለሁና የቂጣውን በዓል ጠብቁት፤ እንግዲህ ይህን ቀን በትውልዳችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት ትጠብቃላችሁ።


የእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ ያድርጉት።


ከኤሊምም ተነሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር፥ በዓሥራ አምስተኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።


የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር በወጡ በሦስተኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።


ኢዮስያስም ለጌታ በኢየሩሳሌም ፋሲካን አከበረ፤ በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን መሥዋዕት አረዱ።


ምርኮኞቹም በመጀመሪያው ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አከበሩ።


አንዱን ጠቦት ጠዋት ሁለተኛውን ጠቦት ደግሞ ማታ ታቀርበዋለህ።


ሁለተኛውን ጠቦት ደግሞ በማታ ታቀርበዋለህ፥ እንደ ጠዋቱም የእህልና የመጠጥ ቁርባን ከእርሱ ጋር ታቀርባለህ፤ ለጌታ መልካም መዓዛ የሚሆን የእሳት ቁርባን ይሆናል።


የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች