እንደ ትላንትና እንዳለፉት ሦስት ቀናት ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረ ጊዜ፥ እስራኤልን በጦርነት የምትመራቸው አንተ ነበርህ፤ ጌታም፥ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”
ዘኍል 27:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም የጌታ ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በእነርሱ ፊት የሚወጣ በእነርሱም ፊት የሚገባ እየመራቸውም የሚያስወጣቸው የሚያስገባቸው ሰው ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ እረኛ እንደሌለው የበግ መንጋ እንዳይሆን በፊቱ የሚወጣና የሚገባ፣ መርቶ የሚያወጣውና የሚያገባው እንዲሆን ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊታቸው የሚወጣውንና የሚገባውን፥ የሚያስወጣቸውንና፥ የሚያስገባቸውንም፥ የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን።” |
እንደ ትላንትና እንዳለፉት ሦስት ቀናት ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረ ጊዜ፥ እስራኤልን በጦርነት የምትመራቸው አንተ ነበርህ፤ ጌታም፥ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”
ሚክያስም “መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኮረብታዎች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ ጌታም ‘እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ ብሏል’ ሲል መለሰለት።”
አቤቱ፥ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል።
ንጉሥ ኢዮአስን በዙሪያው በምትጠብቁበትም ጊዜ ሰይፋችሁን መዛችሁ ወደሚሄድበት ስፍራ ሁሉ አብራችሁ ሂዱ፤ ወደ እናንተ ለመቅረብ የሚደፍር ማንም ቢኖር ይገደል።”
አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት ለመውጣትና ለመግባት እንድችል ጥበብንና እውቀትን ስጠኝ፤ ይህን በሚያህል በዚህ በታላቅ ሕዝብህ ላይ ሊፈርድ የሚችል ማን ነው?”
ሚክያስም እንዲህ አለ፦ “እስራኤል ሁሉ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበትነው አየሁ፤ ጌታም እንዲህ አለ፦ ‘ለእነዚህ ጌታ የላቸውም፥ እያንዳንዱም በሰላም ወደ ቤቱ ይመለስ።’ ”
ተራፊም ትርጒም አልባ ነገር ተናግረዋል፥ ሟርተኞችም ሐሰተኛ ራእይ አይተዋል፤ የሚያሳስቱ ሕልሞችን ተናግረዋል፤ ባዶ ማጽናኛም ሰጥተዋል፤ ለዚህም ነው እረኛም ስለ ሌላቸው እንደ በጎች የተቅበዘበዙትና የተጨነቁት።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።
ኢየሱስ ከጀልባዋ በሚወርድበት ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ አየ፤ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለነበሩም አዘነላቸው፤ ብዙ ነገርም ያስተምራቸው ጀመር።