Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አቤቱ፥ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “አሁንም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ባሪያህ በአባቴ በዳዊት እግር ተተክቼ እንድነግሥ አድርገሃል፤ እኔ ግን ገና ትንሽ ልጅ ስለ ሆንሁ፣ መውጫና መግቢያዬን አላውቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አሁ​ንም አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪ​ያ​ህን በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል፤ እኔም መው​ጫ​ዬ​ንና መግ​ቢ​ያ​ዬን የማ​ላ​ውቅ ታናሽ ብላ​ቴና ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አሁንም፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ! እኔን ባሪያህን በአባቴ በዳዊት ፋንታ አንግሠኸኛል፤ እኔም መውጫውንና መግቢያን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 3:7
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሡም ዳዊት ለጉባኤው ሁሉ እንዲህ አለ፦ “በብቸኛነት እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ብላቴና ለጋ ነው፤ ሕንጻው ግን ለጌታ ለአምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው።


እርሱም የጌታ ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በእነርሱ ፊት የሚወጣ በእነርሱም ፊት የሚገባ እየመራቸውም የሚያስወጣቸው የሚያስገባቸው ሰው ይሁን።


እኔም፦ “ወዮ! ጌታ አምላኬ፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና እንዴት እንደምናገር አላውቅም” አልሁ።


በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፤ ይገባልም፤ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል።


ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!


ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ጌታ መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።


እንደ ትላንትና እንዳለፉት ሦስት ቀናት ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረ ጊዜ፥ እስራኤልን በጦርነት የምትመራቸው አንተ ነበርህ፤ ጌታም፥ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”


መላው እስራኤልና ይሁዳ ግን በፊታቸው እየወጣና እየገባ የሚመራቸው እርሱ ነበርና ዳዊትን ወደዱት።


“እነሆ፤ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከእንግዲህ ልወጣና ልገባ አልችልም፤ ጌታም ‘ዮርዳኖስን አትሻገርም’ ብሎኛል፤


ዳዊትም እንዲህ ብሏልና፦ “ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፥ ለጌታም የሚሠራው ቤት በአገሩ ሁሉ በስሙና በክብሩ እጅግ ታላቅና ዝነኛ ሊሆን ይገባል፤ እኔም ስለዚህ ዝግጅትን አደርጋለሁ።” ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ የግንባታ ቁሳቁስ አዘጋጀ።


እነሆ፥ ልጅ ይወለድልሃል፤ እርሱም ሰላም ያለው ሰው ይሆናል፤ በዙሪያው ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፥ በዘመኑም ሰላምና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ።


ጌታ ግን እንዲህ አለኝ፦ “ ‘ብላቴና ነኝ’ አትበል፤ ወደ ምልክህ ሁሉ ትሄዳለህ፥ የማዝህንም ሁሉ ትናገራለህ።


ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች