ዘኍል 23:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር፥ ለእነርሱ እንደ ጎሽ ቀንድ ያለ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤ ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ ምድር ያወጣቸው እግዚአብሔር እርሱ ለእነርሱ እንደ ጎሽ ቀንድ ይዋጋላቸዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ከግብፅ ያወጣው እርሱ ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ክብር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶአቸዋል፤ ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ነው። |
በወንዙ አጠገብ ባለችው በሕዝቡ ልጆች ምድር በፋቱራ የተቀመጠውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን እዲጠሩት እንዲህ ብሎ መልእክተኞቹን ላከ፦ “እነሆ፥ ከግብጽ የወጣ ሕዝብ አለ፤ እነሆም፥ የምድሩን ሁሉ ፊት ሸፍኖአል፥ በአቅራቢያችንም ተቀምጦአል።
እግዚአብሔርም ከግብጽ አውጥቶታል፤ ጉልበቱ አንደ ጎሽ ቀንድ ያለ ነው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፥ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፥ በፍላጾቹም ይወጋቸዋል።
ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፥ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፥ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፥ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።”
ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ ጌታ የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።