የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 23:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የያዕቆብን ትቢያ ማን ይቈጥራል? የእስራኤልስ አራተኛውን ክፍል ማን ይቈጥራል? የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የያዕቆብን ትቢያ ማን ቈጥሮ ይዘልቃል? የእስራኤልንስ ሩብ ማን ይቈጥረዋል። የጻድቁን ሞት እኔ ልሙት፤ ፍጻሜዬም የርሱ ዐይነት ፍጻሜ ትሁን!”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንደ ትቢያ ብዛት ያላቸውን የያዕቆብ ዘሮች ማን ሊቈጥር ይችላል ወይስ እንደ አዋራ ብናኝ ብዛት ያለውን የእስራኤልን ሩብ ብዛት ማን ሊገምት ይችላል? የጻድቃንን ሞት እንድሞት አድርገኝ መጨረሻዬንም እንደ እነርሱ አድርገው።”

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የያ​ዕ​ቆ​ብን ዘር ማን ያው​ቀ​ዋል? የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንስ ሕዝብ ማን ይቈ​ጥ​ረ​ዋል? ሰው​ነ​ቴም ከጻ​ድ​ቃን ሰው​ነት ጋር ትሙት፤ ዘሬም እንደ እነ​ርሱ ዘር ትሁን።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የያዕቆብን ትቢያ ማን ይቈጥራል? የእስራኤልስ እርቦ ማን ይቈጥራል? የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 23:10
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፥ የምድርን አሸዋን ይቈጥር ዘንድ የሚችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈጠራል።


በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥


ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።


የቅዱሳኑ ሞት በጌታ ፊት የከበረ ነው።


ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም እይ፥ ለሰላም ሰው ተተኪ ይወጣለታልና።


ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል፥ ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል።


ከሮቤል ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ኀምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ ኀምሳ ነበሩ። እነርሱም ቀጥለው ይጓዛሉ።


ከኤፍሬም ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ። እነርሱም ሦስተኛ ሆነው ይጓዛሉ።


ከዳን ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ መቶ ኀምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። እነርሱም በየዓላሞቻቸው በመጨረሻ ይጓዛሉ።”


ከይሁዳ ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነዚህም አስቀድመው ይጓዛሉ።


ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ነገሥታት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት።


የምንኖርበት ምድራዊ ድንኳን የሆነው ሕይወት ቢፈርስ፥ በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ በእጅ ያልተሠራ፥ በእግዚአብሔር የታነጸ መኖሪያ እንዳለን እናውቃለን።


ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ። “ይህንን ጻፍ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።” መንፈስም “አዎን! ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸው ይከተላቸዋልና፤” ይላል።