ማቴዎስ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሲሰድቡአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰዎች በእኔ ምክንያት ቢሰድቧችሁ፣ ቢያሳድዷችሁና ክፉውን ሁሉ በሐሰት ቢያስወሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእኔ ምክንያት ሰዎች ሲሰድቡአችሁና ሲያሳድዱአችሁ፥ በውሸትም ስማችሁን ሲያጠፉት ደስ ይበላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። |
ሞትን ለዘለዓለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ ይህን ጌታ ተናግሮአል።
እናንት በቃሉ ፊት የምትርዱ፥ የጌታን ቃል ስሙ፦ የጠሉአችሁ የናንተው ሕዝብ፥ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ፦ “ደስታችሁን እንድናይ ጌታ ይክበር” ብለዋል፤ ነገር ግን ያፍራሉ።
ደቀመዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባርያም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔልዜቡል ካሉት፥ ቤተሰቦቹንማ እንዴት ከዚህ የበለጠ አይሉአቸው?
ማንም ስለ ስሜ ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘለዓለም ሕይወትንም ይወርሳል።
ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ለሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ በምኵራብ ይገርፏችኋል፤ ምስክር ትሆኑም ዘንድ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸውን በላያችሁ ጭነው ይይዟችኋል፤ ያሳድዱአችኋ፤ ስለ ስሜም ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል፤
እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን።