Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ሆነናል፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ሆናችኋል፤ እንዲሁም እኛ ደካሞች ሆነናል፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ሆናችኋል፤ እናንተ የተከበራችሁ ሆናችኋል፤ እኛ ግን የተዋረድን ሆነናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እኛስ ስለ ክር​ስ​ቶስ ብለን አላ​ዋ​ቂ​ዎች ነን፤ እና​ንተ ግን በክ​ር​ስ​ቶስ ጠቢ​ባን ናችሁ፤ እኛ ደካ​ሞች ነን፤ እና​ንተ ግን ብር​ቱ​ዎች ናችሁ፤ እና​ንተ ክቡ​ራን ናችሁ፤ እኛ ግን የተ​ዋ​ረ​ድን ነን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን እናንተ ግን ኃይለኞች ናችሁ፤ እናንተ የከበራችሁ ናችሁ እኛ ግን የተዋረድን ነን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 4:10
38 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዩም፦ ጓደኞቹ ወደ ሆኑት ወደ ጦር መኰንኖቹ በመጣ ጊዜ “ሁሉ ነገር ሰላም ነውን? ለመሆኑ ይህ እብድ ከአንተ ምን ይፈልጋል?” ሲሉ ጠየቁት። ኢዩም “ሰውየውንም ሆነ እርሱ የሚናገረውን እናንተ ታውቁታላችሁ” አላቸው።


ወዳጁን የሚንቅ ልበ ጐደሎ ነው፥ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል።


የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው፥ ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚያዞርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።


የበቀል ወራት መጥቷል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ይወቀው፤ ከበደልህና ከጥላቻህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሞኝ ሆኗል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።


“በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋልም፤ ስለ ስሜም በሕዝቦች ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።


“ሲሰድቡአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።


“የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም የማይቀበል እኔን አይቀበልም፤ እኔንም የማይቀበል የላከኝን አይቀበልም።”


ጻድቃን ነን በማለት በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤


ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ፥ ሲለዩአችሁና ሲነቅፉአችሁ፥ በክፉም ስማችሁን ሲያጠፉ ብፁዓን ናችሁ!


ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም “ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል?” አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው “አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል፤” አሉ።


የሙታንንም ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ እኩሌቶቹ አፌዙበት፤ እኩሌቶቹ ግን “ስለዚህ ነገር ሁለተኛ እንሰማሃለን፤” አሉት።


እንዲህም ብሎ ስለ ራሱ ሲመልስ ፊስጦስ በታላቅ ድምፅ “ጳውሎስ ሆይ! አብድሃል እኮ፤ ብዙ ትምህርትህ ወደ እብደት ያዞርሃል፤” አለው።


ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና” አለው።


በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በምንሰብከው ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአል።


እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፤


ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፤ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።


ስለዚህ የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።


ፍጥረታዊ ሰው ግን የእግዚአብሔርን መንፈስ ነገር አይቀበለውም፤ ይህ ለእርሱ ሞኝነት ነው፥ ምክንያቱም በመንፈስ የሚመረመር ነውና፥ ሊያውቀው አይችልም።


እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤


ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚህ ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው፥ ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን።


ገና ጠንካራ መብል ለመብላት አልቻላችሁም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ገና አትችሉም፤


አሁንማ ሞልቶላችኋል! አሁንማ ሀብታሞች ሆናችኋል! ያለ እኛ ነግሣችኋል! እኛም ከእናንተ ጋር እንድንነግሥ፥ በእርግጥ ብትነግሡ ኖሮ፥ መልካም በሆነ!


አንዳንዶች “መልእክቶቹ ከባድና ጠንካራ ናቸው፤ ሰውነቱ ሲታይ ግን ደካማ ነው፤ ንግግሩም የተናቀ ነው፤” ይላሉ።


ልባሞች ስለ ሆናችሁ ሞኞችን በደስታ ትታገሣላችሁ!


የሚደክም ማን ነው? እኔም አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው? እኔስ አልናደድምን?


እኛ ስንደክም እናንተም ኀይለኞች ስትበረቱ ደስ ብሎናልና፥ ፍጹማን እንድትሆኑ ደግሞ እንጸልያለን።


ስለዚህ ሞት በእኛ፥ ሕይወት ግን በእናንተ ይሠራል።


በክብርና በውርደት፥ በመመስገንና በመሰደብ ኖረናል። አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤


ስለዚህ ይህን የማይቀበል፥ የማይቀበለው፥ ሰውን ሳይሆን፥ ቅዱስ መንፈሱን ደግሞም የሰጠንን እግዚአብሔርን ነው።


ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ፥ የእግዚአብሔር የክብሩም መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች