ማቴዎስ 18:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነት እላችኋለሁ፥ ባገኘው ጊዜ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነት እላችኋለሁ፤ የጠፋውን በግ ሲያገኝ፣ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በዚያ በተገኘው ደስ ይለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነት እላችኋለሁ፤ ባገኘው ጊዜ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ ጠፍቶ በተገኘው በግ ደስ ይለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል። |
የደከሙትን አላበረታችሁም፥ የታመመውን አላከማችሁትም፥ የተሰበረውን አልጠገናችሁትም፥ የባዘነውን አልመለሳችሁትም፥ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቆና ገዛችኋቸው።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱን ትሩፍ ዓመጽ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ርኅራኄ ይወድዳልና ቁጣውን ለዘለዓለም አያቆይም።