Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 18:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እውነት እላችኋለሁ፤ የጠፋውን በግ ሲያገኝ፣ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በዚያ በተገኘው ደስ ይለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እውነት እላችኋለሁ፥ ባገኘው ጊዜ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እውነት እላችኋለሁ፤ ባገኘው ጊዜ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ ጠፍቶ በተገኘው በግ ደስ ይለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 18:13
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ው​ነቱ ሕማ​ምን ያርቅ ዘንድ ይወ​ዳል፤ ብር​ሃ​ን​ንም ያሳ​የ​ዋል፤ በጥ​በ​ቡም ይለ​የ​ዋል፤ ለጽ​ድ​ቅና ለበጎ ነገር የሚ​ገ​ዛ​ውን ጻድ​ቁን ያጸ​ድ​ቀ​ዋል። የብ​ዙ​ዎ​ች​ንም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን እርሱ ይደ​መ​ስ​ሳል።


ጐል​ማ​ሳም ከድ​ን​ግ​ሊቱ ጋር እን​ደ​ሚ​ኖር፥ እን​ዲሁ ልጆ​ችሽ ከአ​ንቺ ጋር ይኖ​ራሉ፤ ሙሽ​ራም በሙ​ሽ​ራ​ዪቱ ደስ እን​ደ​ሚ​ለው፥ እን​ዲሁ አም​ላ​ክሽ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ዋል።


የደ​ከ​መ​ውን አላ​ጸ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የታ​መ​መ​ው​ንም አል​ፈ​ወ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የጠ​ፋ​ው​ንም አል​ፈ​ለ​ጋ​ች​ሁ​ትም፤ በኀ​ይ​ልና በጭ​ቈ​ናም ገዛ​ች​ኋ​ቸው።


በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።


አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።


“ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን?


እንደዚሁ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም።


ጽድ​ቅን በመ​ሥ​ራት ደስ ያሰ​ኛል እንጂ፥ ግፍን በመ​ሥ​ራት ደስ አያ​ሰ​ኝም።


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች