ኢሳይያስ 53:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ከነፍሱ ሥቃይ ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ አገልጋዬ በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፤ ኃጢአታቸውንም ይሸከማል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ከነፍሱ ሥቃይ በኋላ፣ የሕይወት ብርሃን ያያል፤ ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬ በዕውቀቱ ብዙዎቹን ያጸድቃል፤ መተላለፋቸውንም ይሸከማል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ጻድቁ አገልጋዬ ከሥቃዩ በኋላ የሕይወትን ብርሃን አይቶ ይረካል፤ በዕውቀቱም ብዙዎችን ያጸድቃል፤ በደላቸውንም ይሸከማል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እግዚአብሔርም ከሰውነቱ ሕማምን ያርቅ ዘንድ ይወዳል፤ ብርሃንንም ያሳየዋል፤ በጥበቡም ይለየዋል፤ ለጽድቅና ለበጎ ነገር የሚገዛውን ጻድቁን ያጸድቀዋል። የብዙዎችንም ኀጢአታቸውን እርሱ ይደመስሳል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፥ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውንም ይሸከማል። ምዕራፉን ተመልከት |