ሰቈቃወ 3:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅጥር ሠራብኝ በሐሞትና በድካምም ከበበኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምሬትና በድካም፣ ቅጥር ሠራብኝ፤ ዙሪያዬንም ከበበኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከበባ አድርጎ ምርር ባለ ሐዘንና ችግር ውስጥ ከተተኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዙሪያዬ ቅጥር ሠራብኝ፤ የመከራውንም ጎዳና በእኔ ላይ አቀና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅጥር ሠራብኝ በሐሞትና በድካምም ከበበኝ። |
ስለዚህ ስለ ነብያት የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኩሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና፥ እሬትን አበላቸዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።”
ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? ጌታን ስለ በደልን አምላካችን ጌታ አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።