በዚህም ዓይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ።
ኢያሱ 4:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይኸውም የጌታ እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ፥ አምላካችሁንም ጌታን ለዘለዓለሙ እንድትፈሩ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ያደረገውም፣ የእግዚአብሔር ክንድ ብርቱ መሆኑን የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንዲያውቁና እናንተም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለዘላለም እንድትፈሩ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ምክንያት በምድር ላይ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ እንደ ሆነ ይገነዘባል፤ እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔርን ለዘለዓለም ታከብራላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም የእግዚአብሔር ኀይል ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ፥ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን በሥራው ሁሉ እንድትፈሩ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይኸውም የእግዚአብሔር እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ፥ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ለዘላለሙ እንድትፈሩ ነው። |
በዚህም ዓይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ።
ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።
ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ፤ ኃይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ታላቅ ማድረግ፥ ለሁሉም ኃይልን መስጠት በእጅህ ነው።
ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ ጌታ ሆይ የገዛኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ በኃይልህ ታላቅነት፥ ፍርሃትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፥ እንደ ድንጋይ ቀጥ አሉ።
ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።
አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፤ ጌታ አምላክህን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን፥ ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፤
ጌታ ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እኔ መትቼ እጥልሃለሁ፤ ራስህንም እቆርጠዋለሁ። በዚህች ዕለት የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ሬሣ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ ዓለምም ሁሉ በእስራኤል ዘንድ እግዚአብሔር መኖሩን ያውቃል።