Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 106:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ስለ ስሙ፥ ኃይሉንም ለማስታወቅ አዳናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ ስለ ስሙ አዳናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሆኖም ኀያል ሥልጣኑን ለማሳወቅ ስለ ክብሩ አዳናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 106:8
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአሕዛብን ርስት ይሰጣቸው ዘንድ ለሕዝቡ የሥራውን ብርታት አሳየ።


አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፥ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።


ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።


ቀኝህ ጌታ ሆይ፥ በኃይል ታላቅ ነው፤ አቤቱ፥ ቀኝህ ጌታ ሆይ፥ ጠላትን አደቀቀ።


ሙሴም ጌታ በፈርዖንና በግብጽ ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥ ጌታም እንዳዳናቸው ለአማቱ ተረከለት።


ነገር ግን እንድትቆም ያደረግኩት ኃይሌን እንድገልጥብህና ስሜም በምድር ሁሉ ላይ እንዲታወጅ ነው።


ስለ ስሜ ቁጣዬን አዘገያለሁ፥ እንዳለጠፋህም ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ።


ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፥ የክብርህንም ዙፋን አታዋርድ፤ ከእኛ ጋርም ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስታውስ እንጂ አታፍርስ።


“ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአትን ሠርተናል፤ ምንም እንኳ ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም ስለ ስምህ ብለህ አቤቱ! አድርግ።


ነገር ግን በፊታቸው ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


ነገር ግን እጄን መለስሁ፥ በፊታቸውም ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እንደ ክፉ መንገዳችሁና እንደ ርኩስ ሥራችሁ ሳይሆን ስለ ስሜ ስል በሠራሁላችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ነገር ግን በመካከላቸው ባሉ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


መጽሐፍ ፈርዖንን “ኃይሌ በአንተ እንዲታይ፥ ስሜም በምድር ሁሉ እንዲነገር፥ ለዚህ አስነሣሁህ” ይላልና።


ይኸውም የጌታ እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ፥ አምላካችሁንም ጌታን ለዘለዓለሙ እንድትፈሩ ነው።”


ከነዓናውያንም በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ሰምተው ይከብቡናል፥ ስማችንንም ከምድር ያጠፋሉ፤ ለታላቁ ስምህም የምታደርገው ምንድነው?”


ጌታ የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ስለ ወደደ፥ ስለ ታላቅ ስሙ ሲል ጌታ ሕዝቡን አይተውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች