ኢያሱ 15:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የርሙት፥ ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያርሙት፣ ዓዶላም፣ ሦኮን፣ ዓዜቃ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያርሙት፥ ዐዱላም፥ ሶኮህ፥ ዐዜቃ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርሙት፥ ኤዶላም፥ ሜምብራ፥ ሰአክ፥ አዚቃ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይንገኒም፥ ታጱዋ፥ ዓይናም፥ የርሙት፥ |
አይሁዳዊቱም ሚስቱ የጌዶርን አባት ዬሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።
ጌታም በእስራኤል ፊት አስደነገጣቸው፤ በገባዖንም በጽኑ ውግያ ድል አደረጓቸው፥ በቤትሖሮንም ዐቀበት በሆነው መንገድ ላይ አሳደዳቸው፥ እስከ ዓዜቃና እስከ መቄዳ ድረስ መታቸው።
እንዲህም አደረጉ፤ አምስቱንም ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ የኬብሮንንም ንጉሥ የየርሙትንም ንጉሥ የለኪሶንም ንጉሥ የዔግሎምንም ንጉሥ፥ ከዋሻው ወደ እርሱ አወጡአቸው።
ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም፥ ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ ዔግሎም ንጉሥም ወደ ዳቤር እንዲህ ብሎ ላከ፦