Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 10:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም፥ ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ ዔግሎም ንጉሥም ወደ ዳቤር እንዲህ ብሎ ላከ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ሆሃም ወደተባለው የኬብሮን ንጉሥ ጲርአም ወደተባለው የያርሙት ንጉሥ፣ ያፊዓ ወደተባለው የለኪሶ ንጉሥና ዳቤር ወደተባለው የዔግሎን ንጉሥ በመላክ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለዚህ የኢየሩሳሌሙ ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ሆሃም ተብሎ ለሚጠራው ለኬብሮን ንጉሥ፥ ፒራም ለተባለው ለያርሙት ንጉሥ፥ ያፊዓ ለተባለው ለላኪሽ ንጉሥና ደቢር ለተባለው ለዔግሎን ንጉሥ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስለ​ዚ​ህም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ ወደ ኬብ​ሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የር​ሙት ንጉ​ሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉ​ሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶ​ላም ንጉ​ሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም፥ ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፦ ወደ እኔ ውጡ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 10:3
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በከነዓንም ምድር ባለችው ቂርያት-አርባዕ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ።


እርሱም፦ “ሄደህ ወንድሞችህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፥ ወሬአቸውንም አምጣልኝ” አለው። በዚህ ዓይነት ከኬብሮን ሸለቆ ላከው፥ ወደ ሴኬምም መጣ።


ዳዊት በኬብሮን ነግሶ እስራኤልን የገዛው ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበረ።


ሕዝቅያስም በላኪሽ ሰፍሮ ለነበረው ለሰናክሬም “እኔ በድያለሁ፤ እባክህን አቁም፤ የምትጠይቀኝን ሁሉ እከፍላለሁ” ሲል መልእክት ላከ፤ ንጉሠ ነገሥቱም “እኔ የምፈልገው ዐሥር ሺህ ኪሎ ብርና አንድ ሺህ ኪሎ ወርቅ እንድትልክልኝ ነው” ሲል መለሰለት።


ይህ በዚህ እንዳለ የአሦር ንጉሠ ነገሥት እንደገና የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት ከላኪሽ ተንቀሳቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በመዝመት በሕዝቅያስ ላይ አደጋ እንዲጥልበት አዘዘ፤ ያም ሠራዊት ከፍተኛ ሥልጣን ባላቸው ሦስት የጦር አዛዦቹ የሚመራ ነበር፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ደረሱ ከላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አጠገብ ወደ ልብስ አጣቢዎች መስክ የሚወስደውን መንገድ ያዙ፤


አዶራይምን፥ ለኪሶን፥ ዓዜቃን፥


እንዲህም የተናገረው የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ የቀሩትን ለኪሶንና ዓዜቃንን በወጋ ጊዜ ነበር፤ ከተመሸጉት ከይሁዳ ከተሞች መካከል የተረፉት እነዚህ ብቻ ነበሩና።


በላኪሽ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሠረገላውን ከፈረሱ ጋር አያይዢ፤ እርሷ ለጽዮን ሴት ልጆች የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፤ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።


በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብጽ ካለችው ከጣኔዎእ ከሰባት ዓመት በፊት የተቈረቈረች ከተማ ነበረች።


እንዲህም ሆነ፤ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና በንጉሥዋም ያደረገውን እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ እንዳደረገ፥ የገባዖንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው በመካከላቸውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥


እንዲህም አደረጉ፤ አምስቱንም ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ የኬብሮንንም ንጉሥ የየርሙትንም ንጉሥ የለኪሶንም ንጉሥ የዔግሎምንም ንጉሥ፥ ከዋሻው ወደ እርሱ አወጡአቸው።


ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከለኪሶ ወደ ዔግሎም አለፉ፥ ከበቡአትም፥ ወጉአትም፤


አምስቱም የአሞራውያን ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ የዔግሎም ንጉሥ፥ እነርሱና ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፥ በገባዖንም ዙርያ ሰፈሩ በእርሷም ላይ ጦርነት አደረጉ።


የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት-አርባቅ ትባል ነበር፤ ይህም አርባቅ በዔናቅ ሰዎች መካከል ታላቅ ሰው ነበረ። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።


ሑምጣ፥ ኬብሮን የምትባል ቂርያት-አርባቅ፥ ጺዖር፤ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።


በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።


ጼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባል ኢያቡስ፥ ጊብዓና ቂርያትይዓሪም፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች