ዮሐንስ 4:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቃሉ ምክንያት ከፊተኞች ይልቅ ብዙ ሰዎች አመኑ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቃሉም የተነሣ ሌሎች ብዙዎች አመኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቃሉም ምክንያት ሌሎች ብዙ ሰዎችም በእርሱ አመኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ቃሉም እጅግ ብዙዎች አመኑበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ቃሉ ከፊተኞች ይልቅ ብዙ ሰዎች አመኑ፤ |
ሴቲቱንም “አሁን የምናምነው በቃልሽ ምክንያት አይደለም፤ እኛ እራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱ በእውነት የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን፤” ይሉአት ነበር።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፤” አለ።
ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው።