Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ዕብራውያን 4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ስለ ሰንበት

1 ስለዚህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት ገና ተስፋ ቀርቶልን ከሆነ፥ ከእናንተ ማንም የማይበቃ መስሎ እንዳይታይ እንጠንቀቅ።

2 የምሥራቹ ዜና ለእነርሱም እንደ ተነገረ ለእኛ ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።

3 ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም “እንዲህ ‘ወደ ዕረፍቴ አይገቡም፤’ ብዬ በቁጣዬ ማልሁ፤” እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።

4 ስለ ሰባተኛው ቀን በአንድ ስፍራ፥ “እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ፤” ብሎአልና፤

5 በዚህ ስፍራም ደግሞ “ወደ ዕረፍቴ አይገቡም፤” ይላል፥፥

6 ቀደም ብሎ የምሥራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ምክንያት ስላልገቡ፥ እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ተጠብቆላቸዋል፥

7 ይህም አስቀድሞ እንደተባለው፥ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ፤” በፊት እንደተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ በዳዊት ሲናገር “ዛሬ” ብሎ አንድ ቀን እንደገና ይቀጥራል።

8 ኢያሱ አሳርፎአቸው ኖሮ ቢሆንስ፥ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር።

9 እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።

10 ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።

11 እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።

12 የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፤ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፤ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም አሳብና ትኩረት ይመረምራል፤

13 በፊቱም የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ እኛ መልስ መስጠት በሚገባን ከእርሱ ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው።


ኢየሱስ ታላቁ ሊቀ ካህናት

14 እንግዲህ በሰማያት የወጣ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።

15 እኛ ያለን ሊቀ ካህናት በድካማችን ሊራራልን የሚችል ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር እንደ እኛ ተፈተነ፤ ሆኖም ምንም ኃጢአት አልሠራም።

16 እንግዲህ ምሕረት እንድንቀበልና ርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ጸጋ እንድናገኝ፥ ጸጋው ወደሚገኝበት በመታመን እንቅረብ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች