ንጉሡ አንተን ለማግኘት ፈልጎ በዓለም ላይ መልእክተኛ ያልላከበት አገር እንደሌለ በአምላክህ በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ፤ የአንድ አገር መሪ አንተ በአገሩ ውስጥ አለመኖርክን ባስታወቀው ቍጥር ንጉሥ አክዓብ የአንተን አለመኖር በመሐላ እንዲያረጋግጥለት ጠይቆአል።
ዮሐንስ 18:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና “ማንን ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም የሚደርስበትን ሁሉ ዐውቆ ወጣና፣ “የምትፈልጉት ማንን ነው?” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም የሚደርስበትን ሁሉ ዐውቆ ወደ እነርሱ ወጣ ብሎ “ማንን ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም የሚደርስበትን ሁሉ ዐውቆ ወደ እነርሱ ወደ ውጭ ወጣና፥ “ማንን ትሻላችሁ?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና፦ “ማንን ትፈልጋላችሁ” አላቸው። |
ንጉሡ አንተን ለማግኘት ፈልጎ በዓለም ላይ መልእክተኛ ያልላከበት አገር እንደሌለ በአምላክህ በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ፤ የአንድ አገር መሪ አንተ በአገሩ ውስጥ አለመኖርክን ባስታወቀው ቍጥር ንጉሥ አክዓብ የአንተን አለመኖር በመሐላ እንዲያረጋግጥለት ጠይቆአል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ እንዳለበት ከሽማግሌዎች፥ ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ብዙ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚገደል በሦስተኛውም ቀን እንደሚነሣ ለደቀ መዛሙርቱ ይነግራቸው ጀመር።
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’ ተብሎ ተጽፎአልና፥ በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤
ከዚያም “ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙርም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም ይገባዋል ብዬ የነገርኋችሁ ቃል ይህ ነው፤” አላቸው።
ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን፥ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።
እንግዲህ ክርስቶስ በሥጋ ስለ እኛ መከራን በመቀበሉ፥ እናንተም በዚህ ሐሳብ ራሳችሁን አስታጥቁ፤ ምክንያቱም በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአል።