ኢዩኤል 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይኑ ደርቆአል፥ በለሱም ጠውልጎአል፥ ሮማኑና ተምሩ እንኰዩም የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፥ ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይኑ ደርቋል፤ የበለስ ዛፉም ጠውልጓል፤ ሮማኑ፣ ተምሩና እንኮዩ፣ የዕርሻው ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ ስለዚህ ደስታ፣ ከሰው ልጆች ርቋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን ተክሎችና የበለስ ዛፎች ጠውልገዋል፤ ሮማኑ፥ ተምሩና እንኰዩ፥ ሌሎችም የፍራፍሬ ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ በዚህም ምክንያት በእርግጥ ደስታ ከሰው ልጆች ርቆአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይኑ ደርቆአል፤ በለሱም ጠፍቶአል፤ ሮማኑና ተምሩ፥ እንኮዩም፥ የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይኑ ደርቆአል፥ በለሱም ጠውልጎአል፥ ሮማኑና ተምሩ እንኰዩም የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፥ ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል። |
ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፤ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።
ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፤ የወይ ጠጁን ከወይን መጥመቂያው አጥፍቻለሁ፤ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም።
ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ ሙሉ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ከእነርሱም ሁለት ሰዎች በመሎጊያ ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።